ቀጥታ፡

በሲዳማ ክልል ያሉ እምቅ ሃብቶችን በተደመረ አቅም በማልማት ለዜጎች ተጠቃሚነት ይሰራል

ይርጋለም፣ ጥቅምት 19/2019 (ኢዜአ)፡- በሲዳማ ክልል ያሉ እምቅ ሃብቶችን በተደመረ አቅም በማልማት ለዜጎች ተጠቃሚነት የሚሰራ መሆኑን የክልሉ ርእሰ መስተዳድር መሳይ ሃይሉ (ዶ/ር) ገለጹ።

ርእሰ መስተዳድሩ በመደመር መንግሥት የተያዙ የልማት እቅዶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ በይርጋለም ከተማ ከነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል።


 

በሲዳማ ክልል ለግብርና ምርቶች፣ ለአትክልትና ፍራፍሬ፣ ለዓሳ እና ሌሎችም የልማት ስራዎች እምቅ አቅም መኖሩን አንስተዋል።

በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍና ሌሎችም የኢንቨስትመንት መስኮች በክልሉ ብዙ መስራትና ውጤታማ መሆኑን የሚቻል መሆኑንም አንስተዋል።

በመሆኑም በክልሉ ያሉ እምቅ ሃብቶችን በተደመረ አቅም በማልማት ለዜጎች ተጠቃሚነት የሚሰራ መሆኑን  ተናግረዋል።

በዚህ ረገድ የአመራሩ ቁርጠኝነት እንዳለ ሆኖ የህዝቡ እገዛ፣ ትብብርና የልማት ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።

የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች መፍታት፣ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልገሎት መስጠት የመንግስት አይነተኛ ትኩረት ሆኖ የሚቀጥል መሆኑንም ርእሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።

በውይይት መድረኩ ከዞኑ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና በየደረጃው ያሉ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም