ቀጥታ፡

ኤቨርተን ወይስ ኒውካስትል? የመጨረሻውን የካራባኦ ካፕ የሩብ ፍጻሜ ትኬት ማን ይቆርጣል?

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 19/2019 (ኢዜአ) ፦  የካራባኦ ካፕ የአራተኛ ዙር የመጨረሻ መርሐ ግብር በኤቨርተን እና ኒውካስትል ዩናይትድ መካከል ዛሬ ይደረጋል። 

የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ከ45 ላይ በሂል ዲኪንሰን ስታዲየም ይካሄዳል።

በሶስተኛ ዙር የውድድሩ መርሐ ግብር ኤቨርተን ዎልቭስን፣ ኒውካስትል ዩናይትድ ሚልዎልን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል።

ኤቨርተን የካራባኦ ካፕ ዋንጫን አንስቶ አያውቅም። በሁለት አጋጣሚ ለፍጻሜ ደርሶ ሽንፈት አስተናግዷል።

ኒውካስትል ዩናይትድ በ2017 ዓ.ም ሊቨርፑልን 2 ለ 1 በማሸነፍ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን አንስቷል።

ሁለቱ ክለቦች በካራባኦ ካፕ ከዚህ ቀደም የተገናኙት አንድ ጊዜ ብቻ ነው።

እ.አ.አ በ2002/03 ባደረጉት የሶስተኛ ዙር ጨዋታ ኤቨርተን በመለያ ምት ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

የዛሬው ጨዋታ አሸናፊ ክለብ በሩብ ፍጻሜ የመጨረሻውን ቦታ ያገኛል።

ሊቨርፑል፣ ማንችስተር ሲቲ፣ ቦርንማውዝ፣ ሰንደርላንድ፣ ክሪስታል ፓላስ፣ ፍሊትውድ ታውን እና ብራድፎርድ ሲቲ ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀሉ ክለቦች ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም