ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር) ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 19/2019(ኢዜአ) ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂጃለሁ ብለዋል።


 

ውይይታቸው በኒውክሊየር ኃይል፣ በጤናና ንግድ ዘርፎች ያለውን ትብብር እንዲሁም በጋራ ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮችን ያካተተ እንደነበረም ገልጸዋል።

በተጨማሪም፣ ለውይይት፣ ለጋራ መግባባት እና ለኢትዮጵያ-ሩሲያ ግንኙነት ቀጣይነት ያለው እድገት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያሳየውን የመደመር መጽሐፌን የሩሲያኛ ዕትም ለፕሬዚዳንት ፑቲን አበርክቼላቸዋለሁ ብለዋል።

#ትልቅሀገር፣ #ትልቅሕዝብ፣ #ታላቅርዕይ #Ethiopia #Russia

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም