ቀጥታ፡

ሊቨርፑል እና ማንችስተር ሲቲ በካራባኦ ካፕ ለሩብ ፍጻሜ አለፉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19/2019 (ኢዜአ)፦ በካራባኦ ካፕ የአራተኛ ዙር መርሐ ግብር ትናንት ማምሻውን አምስት ጨዋታዎች ተደርገዋል።

በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ተጠባቂ ጨዋታ ሊቨርፑል ቼልሲን በመለያ ምት አሸንፏል።

ሁለቱ ቡድኖች በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ኮዲ ጋፕኮ ለሊቨርፑል፣ ሞርጋን ሮጀርስ ለቼልሲ በተመሳሳይ ጎሎቹን በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥረዋል።

የጨዋታውን አሸናፊ በመለያ ምት የተለየ ሲሆን ሊቨርፑል 6 ለ 5 በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ አልፏል።

በሌላኛው መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ብራይተንን ረትቷል።

በኢትሃድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ በ90 ደቂቃ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

ማቴዎ ኮቫቺች እና ቪቶር ሬስ ለሲቲ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ጆርጂኒዮ ሩተር እና ማሊክ ጁኒየር ያልኩዬ ለብራይተን ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ጨዋታው በመደበኛ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት በመጠናቀቁ ምክንያት ወደ መለያ ምት አምርቷል።

በዚህም ማንችስተር ሲቲ 4 ለ 3 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።

ቦርንማውዝ አስቶንቪላን 3 ለ 0፣ ሰንደርላንድ ብሬንትፎርድን 3 ለ 2 እና ክሪስታል ፓላስ ፉልሃምን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ አልፈዋል።

የካራባኦ ካፕ የአራተኛ ዙር መርሐ ግብር ኤቨርተን እና ኒውካስትል ዩናይትድ ዛሬ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም