ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በታላቁ የክሬምሊን ቤተ መንግሥት አቀባበል አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በታላቁ የክሬምሊን ቤተ መንግሥት አቀባበል አደረጉ
አዲስ አበባ ጥቅምት 18/2019(ኢዜአ)፦ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን በታላቁ የክሬምሊን ቤተ መንግሥት አቀባበል አድርገዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን በሞስኮ እየተካሄደ ያለውን 3ኛውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ አስመልክቶ በታላቁ የክሬምሊን ቤተ መንግሥት በተዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ መቀበላቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስታውቋል።