ቀጥታ፡

አርሰናል ባልተጠበቀ ሁኔታ በአራተኛ ዲቪዚዮን ክለብ ፍሊትውድ ተሸንፎ ከካራባኦ ካፕ ውድድር ውጪ ሆኗል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019 (ኢዜአ)፦ በካራባኦ ካፕ የአራተኛ ዙር መርሐ ግብር ፍሊትውድ ታውን አርሰናልን በመለያ ምት  አሸንፏል።

ማምሻውን በሃይበሪ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አሮን ሉፓሎቢ በ21ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ፍሊትውድ መሪ ሆኗል።

ቪክቶር ዮኮሬስ በ50ኛው ደቂቃ ለአርሰናል የአቻነቷን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።


የአርሰናሉ ታዳጊ ማክስ ዶውማን በ85ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል። ጨዋታው በመደበኛ ክፍለ ጊዜ በአቻ ውጤት በመጠናቀቁ ወደ መለያ ምት አምርቷል።

በዚህም ፍሊትውድ ታውን 5  ለ 3 በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ አልፏል። ብሩኖ ጉማራሽ ከአርሰናል ፍጹም ቅጣት ምት ስቷል።

የወቅቱ የሊጉ ሻምፒዮን አርሰናል ማንም ባልተጠበቀው ሁኔታ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል። ይህም የውድድሩ ያልተጠበቀ ሆኖ ተመዝግቧል።

በሊግ ቱ (በአራተኛው የሊግ እርከን)  የሚገኘው ፍሊትውድ ታውን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሩብ ፍጻሜ አልፏል።

ፍሊትውድ በሊግ ቱ 18ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በሌላኛው መርሐ ግብር ብራድፎርድ ሲቲ ፒተርቦሮውን 2 ለ 0 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም