ሊቨርፑል ከቼልሲ እና ማንችስተር ሲቲ ከብራይተን ፡ የካራባኦ ካፕ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች - ኢዜአ አማርኛ
ሊቨርፑል ከቼልሲ እና ማንችስተር ሲቲ ከብራይተን ፡ የካራባኦ ካፕ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2019(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ አራተኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ አምስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ምሽት አምስት ላይ ሊቨርፑል ከቼልሲ በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
በሶስተኛ ዙር ሊቨርፑል ቶተንሃም ሆትስፐርስን 3 ለ 1፣ ቼልሲ ሊድስ ዩናይትድን 6 ለ 3 አሸንፈዋል።
ሊቨርፑል 10 ጊዜ ውድድሩን በማሸነፍ ስኬታማው ክለብ ነው። ተጋጣሚው ቼልሲ አምስት ጊዜ ዋንጫውን አንስቷል።
ሁለቱ ክለቦች ከዚህ ቀደም በካራባኦ ካፕ (በቀድሞ አጠራሩ የሊግ ካፕ) ስምንት ጊዜ የተገናኙ ሲሆን ከነዚህም ሶስቱ የፍጻሜ ጨዋታዎች ናቸው።
ሊቨርፑል ከሶስቱ የፍጻሜ ጨዋታዎች ሁለቱን ሲያሸንፍ ቼልሲ በቀሪው ጨዋታ ድል ቀንቶታል።
እ.አ.አ በ2024 በውድድሩ ለመጨረሻ ጊዜ በተገናኙበት የፍጻሜ ጨዋታ ሊቨርፑል 1 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል።
በአጠቃላይ ከስምንቱ ጨዋታዎች ቼልሲ በአራቱ ሲያሸንፍ ሊቨርፑል ሁለት ጊዜ ድል ቀንቶታል። በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ብራይተንን ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ላይ በኢትሃድ ስታዲየም ያስተናግዳል።
በሶስተኛ ዙር መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ኖርዊች ሲቲን 5 ለ 0 ሲረታ ብራይተን ማንችስተር ዩናይትድን 3 ለ 2 አሸንፏል።
ማንችስተር ሲቲ ስምንት ጊዜ ካራባኦ ካፕን ስምንት ጊዜ በማንሳት ከሊቨርፑል በመቀጠል ስኬታማው ክለብ ነው። የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊም ነው።
ብራይተን በውድድሩ ትልቁ ውጤቱ ሩብ ፍጻሜ ሲሆን ይህም የሆነው በ1978/79 የውድድር ዓመት ነበር።
ሁለቱ ክለቦች እ.አ.አ በ2008 በተገናኙበት ብቸኛ አጋጣሚ ብራይተን ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
ጨዋታዎቹ ተመጣጣኝ ፉክክር ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
በሌሎች መርሐ ግብሮች ቦርንማውዝ ከአስቶንቪላ፣ ፉልሃም ከክሪስታል ፓላስ እና ሰንደርላንድ ከብሬንትፎርድ በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ከ45 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።