ቀጥታ፡

መቻል የሊጉ መሪ ሆነ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ኢትዮጵያ መድንን 3 ለ 1 ረትቷል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቸርነት ጉግሳ፣ ፈቱዲን ጀማል (ፍጹም ቅጣት ምት) እና መሐመድ አበራ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ናይጄሪያዊው አማኑኤል ኦሊሳ የኢትዮጵያ መድንን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

በሊጉ ሶስተኛ ድሉን ያስመዘገበው መቻል በዘጠኝ ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አንደኛ ከፍ አድርጓል።

በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ መድን በአራት ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ አንድ ቀሪ ጨዋታ አለው።

ጨዋታውን ተከትሎ የአራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ተጠናቋል።

የአምስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከጥቅምት 20 2019 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም