ቀጥታ፡

ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ለዜጎች ሰላምና ደህንነት መከበር ሁሌም ዝግጁ ነን- የሰራዊቱ መኮንኖች

ሀረር፣ ጥቅምት 16/2019 (ኢዜአ)፡-ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ለዜጎች ሰላምና ደህንነት መከበር ሁሌም ዝግጁ ነን ሲሉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ገለጹ።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለየትኛውም ሀገራዊ ተልእኮ እና ግዳጅ ዝግጁ በመሆን በብቃት፣ በጀግንነትና በቆራጥነት እየፈፀመ ይገኛል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከሀገር አልፎ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር ተልእኮ የካበተ ስምና ዝና ያለው ሰራዊት መሆኑም ይታወቃል።

ለየትኛውም ሀገራዊ ተልእኮ እና ግዳጅ ዝግጁ በመሆን በብቃት፣ በጀግንንትና በቆራጥነት እየፈፀመ ይገኛል።

ከዚሁ ጋር በተገናኘ ኢዜአ ያነጋገራቸው በሀገር መከላከያ ሰራዊት የምስራቅ እዝ ከፍተኛና መካከለኛ መኮንኖች፤ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ለዜጎች ሰላምና ደህንነት መከበር ሁሌም ዝግጁ ነን ብለዋል።

ከከፍተኛ መኮንኖች መካከል ሌተናል ኮሎኔል ክንዴ ጥላሁን፤ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀገርንና የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ በጀግንነትና በቆራጥነት አደራውን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል።

ለሀገር ሉአላዊነት፣ ለብሄራዊ ጥቅሟ መከበርና ለቀጣናው ሰላም የሚሰራ ብቁና ጠንካራ ሰራዊት የተገነባ መሆኑንም ተናግረዋል።


 

ሌላኛው የእዙ መኮንን የሆኑት ሻምበል በያን ሰዒድ፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በዘመናዊ ትጥቁና አደረጃጀቱ፣ በጀግንነቱ፣ በውጊያ ብቃቱ ጠንካራና አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል። 


 

በመሆኑም ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት መከበር፣ ለብሄራዊ ጥቅሟ መጠበቅ ሁሌም በላቀ ዝግጁነት ላይ እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላኛው አስተያየት ሰጪ መቶ አለቃ አሻግሬ አሸናፊ፤ ለየትኛውም ግዳጅና ተልእኮ የተዘጋጀ ብቁና አስተማማኝ ሰራዊት መገንባቱን ተናግረዋል።

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም