በካራባኦ ካፕ አርሰናል ከፍሊትውድ ታውን ጋር ይጫወታል - ኢዜአ አማርኛ
በካራባኦ ካፕ አርሰናል ከፍሊትውድ ታውን ጋር ይጫወታል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2019 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ አራተኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል።
ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በሀይበሪ ስታዲየም ፍሊትውድ ታውን አርሰናልን ያስተናግዳል።
በሊግ ቱ (የእንግሊዝ አራተኛ የሊግ እርከን) የሚገኘው ፍሊትውድ ታውን በሶስተኛው ዙር ሼፍልድ ዩናይትድን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ክለቡ ወደ አራተኛው ዙር ሲያልፍ በካራባኦ ካፕ ተሳትፎው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ተጋጣሚው አርሰናል በሶስተኛው ዙር ኤፕስዊች ታውንን 4 ለ 2 በመርታት 16ቱን ተቀላቅሏል።
ሁለቱ ክለቦች እርስ በእርስ ሲገናኙ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
አርሰናል የማሸነፉን ከፍተኛ ግምት ወስዷል።
መድፈኞቹ ለመጨረሻ ጊዜ ዋንጫውን ያነሱት እ.አ.አ በ1993 የውድድር ዓመት ነው።
የጨዋታው አሸናፊ ወደ ሩብ ፍጻሜ ያልፋል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ብራድፎርድ ሲቲ ከፒተርቦሮው ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በኖርዝ ኮሜርሻልስ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የካራባኦ ካፕ የአራተኛ ዙር መርሐ ግብር እስከ ጥቅምት 19 2019 ዓ.ም ይቆያል።
አሸናፊ ክለቦች ሩብ ፍጻሜውን ይቀላቀላሉ።