ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ኳታር በወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 16/2019 (ኢዜአ) ፦የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሰይድ ሙባረክ ሰይድ አሊ ጃፋር አልሚኖ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሩ ኳታር በቅርብ ጊዜ  በሽብር ኃይሎች ጥምረት የሀገርን እና  የኢትዮጵያን  ህዝብ ሰላም ለማደፍረስ ዓላማ ያደረገውን ጦርነት አስመልክቶ የሰጠችው ፍትሃዊ እና ጠንካራ መግለጫ ሀገሪቱ ከእውነት ጎን ለመቆም ያላትን ቁርጠኝነት ያመላከተ መሆኑን በመግለጽ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በቀጣይም በሀሉቱ ሀገራት መካከል የሚደረገውን ወታደራዊ ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር መስራት እንደሚገባ በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡

አምባሳደር ሰይድ ሙባረክ ሰይድ አሊ ጃፋር አልሚኖ በበኩላቸው፤ ወይይቱ ከአዲሱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ ጋር ለመተዋወቅ እና በቀጣይም የሁለቱን ሀገራት ወታደራዊ እና ሁለንተናዊ ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በር እንደከፈተላቸው ገልጸዋል።

በቀጣናዊ እና በዓለም አቀፋዊ የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ የሁለቱንም ሀገራት ክብር እና ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ የሚችሉ ልዩ ልዩ ወታደራዊ ትብብሮችን ለማድረግ ጠቃሚ ውይይት በማደረጋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ከመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም