ኢትዮ ኤሌክትሪክ ዓመቱን በድል ጀምሯል - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ዓመቱን በድል ጀምሯል
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 16/2019 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቤተልሄም መንተሎ በ47ኛው ደቂቃ ግቡን አስቆጥራለች።
ውጤቱን ተከትሎ አምና ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የመጀመሪያ ሶስት ነጥቡን አግኝቷል።
ድሬዳዋ ከተማ ሊጉን በሽንፈት ጀምሯል።
ጨዋታውን ተከትሎ የአንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር ተጠናቋል።