ጋሞ ጨንቻ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ጋሞ ጨንቻ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 16/2019 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት ጨዋታ ጋሞ ጨንቻ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አባያ ካምፓስ ስታዲየም ተካሄዷል።
በሊጉ የመጀመሪያ ነጥቡን ያገኘው ጋሞ ጨንቻ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ይቀረዋል።
በተከታታይ ጨዋታዎች አቻ የወጣው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በስምንት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን መሪነቱን ለነገሌ አርሲ አስረክቧል።
በአምተኛ ሳምንት ጋሞ ጨንቻ ከሀዋሳ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ መድን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።