ቀጥታ፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ሲጥል ነገሌ አርሲ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 16/2019 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሸገር ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አማኑኤል ኤርቦ እና ናትናኤል ዳንኤል ለቅዱስ ጊዮርጊስ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

አሚር አብዶ እና ቢኒያም ፍቅሩ የሸገር ከተማን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።


ቅዱስ ጊዮርጊስ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን የማስመዝገብ እድሉን አልተጠቀመበትም። እስከ አሁን ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ያገኘው ሶስት ነጥብ ብቻ ነው።

በውድድር ዓመቱ ለሁለተኛ ጊዜ አቻ የወጣው ሸገር ከተማ ነጥቡን ወደ አምስት ከፍ አድርጓል።

በአምስተኛ ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ሸገር ከተማ ከነገሌ አርሲ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በሌላኛው መርሐ ግብር ነገሌ አርሲ አዳማ ከተማን 1 ለ 0 ረትቷል።


በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ካሜሮናዊው የመሐል ተከላካይ ዴዚሬ ፓስካል በ33ኛው ደቂቃ ጎሉን አስቆጥሯል።

ነገሌ አርሲ በሊጉ ሁለተኛ ድሉን ሲያስመዘግብ አዳማ ከተማ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም