ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በጀርመን እና በአየርላንድ የማራቶን ውድድሮች ድል ተቀዳጁ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በጀርመን እና በአየርላንድ የማራቶን ውድድሮች ድል ተቀዳጁ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 16/2019(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በጀርመን እና በአየርላንድ በተካሄዱ ማራቶኖች በሁለቱም ጾታዎች የውድድሩ አሸናፊ በመሆን ደምቀዋል።
በጀርመን በተደረገው የፍራንክፈርት ማራቶን በወንዶች ምድብ አትሌት ጂራ ታሌሊሳ የራሱን የግል ምርጥ ሰዓት በማሻሻል 2 ሰዓት ከ05 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ አሸናፊ ሆኗል።
በወንዶች ምድብ የተሳተፈው አትሌት አቤ ጋሻሁን 2 ሰዓት ከ07 ደቂቃ ከ19 ሰከንድ በመግባት 6ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
በዚሁ የፍራንክፈርት ማራቶን በሴቶች ምድብ አትሌት ዘይነባ ይመር 2 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ45 ሰከንድ አሸንፋለች።
አትሌት በሪሃ ገብረ ዮሐንስ በ2:22:46 3ኛ፣ አትሌት አሰለፍ አማረ 2:25:31 4ኛ፣ አትሌት ስራነሽ ይርጋ 2:26:05 5ኛ፣ አትሌት ምህረት ገመዳ 2:26:49 6ኛ፣ እንዲሁም አትሌት ብርቄ በየነ 2:31:00 9ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።
በተያያዘም በአየርላንድ በተካሄደው የደብሊን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች አሸንፈዋል።
በወንዶች ምድብ አትሌት አባይ አለሙ 2 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ከ29 ሰከንድ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቋል።
በሴቶች ምድብ ደግሞ አትሌት ዘነቡ ፍቅዳው 2 ሰዓት ከ24 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ የደብሊን ማራቶን አሸናፊ መሆኗን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመለክታል።