ቀጥታ፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከድሬዳዋ ከተማ ፤ የመጀመሪያ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 16/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከድሬዳዋ ከተማ  በአበበ ቢቂላ  ስታዲየም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

አምና እስከ መጨረሻው ሳምንት ዋንጫ ለማንሳት ፉክክር ያደረገው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ66 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

ተጋጣሚው ድሬዳዋ ከተማ ባለፈው የውድድር ዓመት በ28 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ይዞ መጨረሱ የሚታወስ ነው።

ሁለቱ ክለቦች በ2018 ዓ.ም ባደረጓቸው የእርስ የእርስ የሊግ ጨዋታዎች ኢትዮ ኤሌክትሪክ በማሸነፍ ከተጋጣሚው ስድስት ነጥብ ወስዷል።

ባለፈው የውድድር ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ በተገናኙበት የ17ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።

ዙፋን ደፈርሻ፣ ማህሌት ምትኩ እና ዳግማዊት ሰለሞን የማሸነፊያ ግቦቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።

ዝናሽ ሰለሞን ለድሬዳዋ ከተማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።

ሁለቱ ቡድኖች ዓመቱን በድል ለመጀመር ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም