ቦሌ ክፍለ ከተማ እና ጉለሌ ክፍለ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል - ኢዜአ አማርኛ
ቦሌ ክፍለ ከተማ እና ጉለሌ ክፍለ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 16/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ትናንት ተደርገዋል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተከናወነው ጨዋታ ቦሌ ክፍለ ከተማ መቻልን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ሊድያ ሰለሞን እና ትርሲት ወንድወሰን ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ትንቢተ ሳሙኤል የመቻልን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
ጉለሌ ክፍለ ከተማ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 0 ረትቷል።
በሃዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ በተካሄደው ጨዋታ ፍጹም ፈለሀ ግቦቹን አስቆጥራለች።
በሌሎች መርሐ ግብሮች አዳማ ከተማ ከልደታ ክፍለ ከተማ ያለ ግብ አቻ ሲለያዩ አዲስ አዳጊው ጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከል እና ሸገር ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ሶስት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
በሊጉ መክፈቻ ቀን በተደረጉ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይርጋጨፌ ቡናን 2 ለ 0፣ ሀዋሳ ከተማ ባህር ዳር ከተማን 2 ለ 1 አሸንፈዋል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከድሬዳዋ ከተማ ዛሬ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል።