ቀጥታ፡

በኤል ክላሲኮ ደርቢ ሪያል ማድሪድ ባርሴሎናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 16/2019 (ኢዜአ)፦ በስፔን ላሊጋ የ10ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ ባርሴሎናን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ትናንት ማምሻውን በካምፕ ኑ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኪሊያን ምባፔ በ41ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል ማድሪድን መሪ አድርጓል።

ራፊኒሃ በ61ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፈው ጎል ባርሴሎና አቻ ሆኗል።

ይሁንና በ87ኛው ደቂቃ ኪሊያን ምባፔ ባስቆጠረው ጎል ማድሪድ ጣፋጭ ድል ተቀዳጅቷል።

265ኛው የኤል ክላሲኮ ደርቢ በሪያል ማድሪድ አሸናፊነት ተጠናቋል።

ሪያል ማድሪድ በ24 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን የያዘ ሲሆን ከባርሴሎና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት ዝቅ አድርጓል።

በሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው ባርሴሎና በ27 ነጥብ አሁንም ሊጉን እየመራ ነው።

በ11ኛ ሳምንት ባርሴሎና ከዲፖርቲቮ አላቬስ፣ ሪያል ማድሪድ ከሬሲኒግ ሳንታንዴር ጋር ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም