ሲዳማ ቡና ከካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ውጭ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
ሲዳማ ቡና ከካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ውጭ ሆነ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 16/2019 (ኢዜአ):- በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ ሲዳማ ቡና በሱዳኑ አል ሂላል ኦምዱርማን የ2 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዷል።
ትናንት ማምሻውን በሩዋንዳ አማሆሮ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ መሐመድ አብዱልራህማን እና አርነስት ሉዞሎ ሲታ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና በድምር ውጤት 4 ለ 0 ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል።
የሱዳኑ አል አህሊ ኦምዱርማን በበኩሉ የምድብ ድልድል ተሳትፎውን አረጋግጧል።
የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች ከህዳር ወር 2019 ዓ.ም ይካሄዳሉ።