ሊቨርፑል ድል ሲቀናው ማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናገደ - ኢዜአ አማርኛ
ሊቨርፑል ድል ሲቀናው ማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናገደ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሊቨርፑል ብራይተንን 2 ለ 0 ረቷል፡፡
በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አሌክሳንደር ኢሳቅ እና የብራይተኑ ፓስካል ግሮስ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በውድድር ዓመቱ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሊቨርፑል በ15 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል።
ሊቨርፑል በአንፊልድ የመጀመሪያ ድሉን አሳክቷል።
በአንጻሩ በሊጉ ሁለተኛ ሽንፈት ያስተናገደው ብራይተን በ16 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ቦርንማውዝ ማንችስተር ዩናይትድን 3 ለ 0 ረትቷል።
በኦልትራፎርድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ራያን፣ ማርከስ ታቨርኒየር እና ኢቫኒልሰን ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በሊጉ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ማንችስተር ዩናይትድ በሰባት ነጥብ ከነበረበት 15ኛ ደረጃ ወደ 16ኛ ዝቅ ብሏል።
ዩናይትድ ባለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች ከድል ርቋል።
ሽንፈቱን ተከትሎ የክለቡ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ሊሰናበቱ ይችላሉ የሚሉ መረጃዎች በስፋት እየወጡ ነው።
ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ቦርንማውዝ በዘጠኝ ነጥብ ደረጃውን ከ17ኛ ወደ 13ኛ ከፍ አድርጓል።
በሌሎች መርሐ ግብሮች ኒውካስትል ዩናይትድ ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 0 ሲረታ ሁል ሲቲ እና ብሬንትፎርድ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር በሰንደርላንድ እና ሊድስ ዩናይትድ መካከል ምሽት 1 ሰዓት ከ30 በስታዲየም ኦፍ ላይት ይደረጋል።