ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ቡና ተከታታይ ሽንፈት አስተናገደ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አቤል ሀብታሙ በመጀመሪያ አጋማሽ ግቡን አስቆጥሯል።

በሊጉ ተከታታይ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በሶስት ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል። 

ቡናማዎቹ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

በአንጻሩ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሰባት ነጥብ ደረጃውን ከ8ኛ ወደ 2ኛ ከፍ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም