የወቅቱ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓመቱን በድል ጀምሯል - ኢዜአ አማርኛ
የወቅቱ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓመቱን በድል ጀምሯል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ)፦ የ2019 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ጅማሮውን አግኝቷል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይርጋጨፌ ቡናን 2 ለ 0 አሸንፏል።
እፀገነት ግርማ ግቦቹን አስቆጥራለች።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዋንጫ ክብሩን የማስጠበቅ ጉዞውን በአሸናፊነት ጀምሯል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ባህር ዳር ከተማን 2 ለ 1 ረትቷል።
ቤተልሄም ታምሩ እና ታደለች አብርሃም ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ዳሳሽ ሰውአገኝ የባህር ዳር ከተማን ግብ አስቆጥራለች።