ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ቡና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ : የዕለቱ ተጠባቂ መርሐ ግብር

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ  አራተኛ ሳምንት  ብቸኛ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክን ያገናኛል።

ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክን  በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ከሶስት ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ ያገኘው ኢትዮጵያ ቡና 11ኛ ደረጃን ይዟል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በተመሳሳይ ሶስት ነጥብ በግብ ክፍያ በልጦ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር በነገሌ አርሲ የ3 ለ 0 ሽንፈት ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሶስተኛ ሳምንት ሸገር ከተማን 1 ለ 0 በመርታት በሊጉ የጀመሪያ ድሉን አሳክቷል። ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ፍልሚያ ያደርጋል።

ሁለቱ ክለቦች ባለፈው የውድድር ዓመት በሊጉ ባደረጓቸው ጨዋታዎች ኢትዮ ኤሌክትሪክ  በማሸነፍ ስድስት ነጥብ ወስዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም