ሊቨርፑል ከብራይተን፣ ማንችስተር ዩናይትድ ከቦርንማውዝ፦ የዛሬ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታዎች - ኢዜአ አማርኛ
ሊቨርፑል ከብራይተን፣ ማንችስተር ዩናይትድ ከቦርንማውዝ፦ የዛሬ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታዎች
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል።
በዕለቱ አምስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ከቀኑ 11 ሰዓት ሊቨርፑል ከብራይተን በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ባለሜዳው ሊቨርፑል በ12 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። ብራይተን በ16 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ብሬንትፎርድን 2 ለ 1 ያሸነፈው ሊቨርፑል ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል።
ባለፉት አራት የሊግ ጨዋታዎች ያሸነፈው እና በውድድር ዓመቱ አስደናቂ አጀማመር ያሳየው ብራይተን በድል ጉዞው ለመጠቀል ፍልሚያ ያደርጋል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ቦርንማውዝን ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ያስተናግዳል።
ማንችስተር ዩናይትድ በሰባት ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ከድል በመራቅ የውጤት ማጣት ቀውስ ውስጥ ይገኛል።
ቦርንማውዝ በስድስት ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በሰባተኛ ሳምንት ሰንደርላንድን 2 ለ 0 በማሸነፍ የመጀመሪያ ድሉን አሳክቷል።
ባለሜዳው ዩናይትድ ከጫና ለመውጣት የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ግድ ይለዋል። ተጋጣሚው ቦርንማውዝ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይፋለማል።
በሌሎች መርሐ ግብሮች ክሪስታል ፓላስ ከኒውካስትል ዩናይትድ እና ሁል ሲቲ ከብሬንትፎርድ በተመሳሳይ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የስምንተኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር በሰንደርላንድ እና በሊድስ ዩናይትድ መካከል ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ በስታዲየም ኦፍ ላይት ይካሄዳል።