ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጀግንነትን በልቡ ያነገሰ የሀገር ሉዓላዊነት ዘብ ነው 

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 14/2019 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጀግንነትን በልቡ ያነገሰ የሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ጋሻ፤ የሀገር ሉዓላዊነት ጽኑ ዘብ መሆኑን የቀድሞ የባሕር ኃይል አባል ሌፍተናንት ኮማንደር መረባ አቶምሳ ገለጹ።

ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብና ታላቅ ርዕይ

የሰራዊት ቀን የመከላከያ ሰራዊት በዘመናዊ መልኩ ጥቅምት 15 ቀን 1900 ዓ.ም የተመሰረተበትን ታሪክ በማሰብ ይከበራል።

በዓሉ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የጦር ሚኒስትር የሰየመችበትን ቀን በማስታወስ ለሀገር ሉዓላዊነት መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖች ይዘከሩበታል።

የበዓሉ ዓላማም የሰራዊቱን ጀግንነት፣ ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ሚና እና አኩሪ ታሪክ ለታላቁ ትውልድ በቅብብሎሽ ማስተላለፍ ነው።

የዘንድሮው 119ኛው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ቀን “የድል ሰራዊት” በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል።

ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የቀድሞ የባሕር ኃይል አባል ሌፍተናንት ኮማንደር መረባ አቶምሳ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሳይታጠቅ እንኳን ወኔው በዓለም የታወቀ መሆኑን ገልጸዋል።

ሰራዊቱ የማንንም ሀገር ለመውረር ተነስቶ እንደማያውቅ ገልጸው፣ ለመውረር የመጡትን ደግሞ አሳፍሮ መመለሱን ጠቁመዋል።

ሰራዊቱ እንደ ዛሬው ዘመናዊ መሳሪያ ሳይታጠቅ እንኳን በዓለም ስሙ የታወቀ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት በማረጋገጥና የሀገርን ሉዓላዊነት በመጠበቅ ዛሬም እንደ ትናንቱ ጸንቶ የቆመ ኃይል መሆኑን አንስተዋል።

119ኛውን የሰራዊት ቀን ስናከብር ሰራዊቱ በቀጣይ የሚያስመዘግባቸው ድርብ ድሎችን እያሰብን ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም