ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር በመሆን የባሕር ዳር ስታዲየምን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 14/2019 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ መሪዎችና ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በመሆን የባሕር ዳር ስታዲየምን ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ከ12ኛውን የጣና ፎረም ከታደሙ በኋላ፣ ከአፍሪካ መሪዎችና ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በመሆን ባሕር ዳር ስታዲየምን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።


 

ጉብኝቱ በስፖርት መሠረተ ልማት ረገድ ያለውን መሻሻል እንዲሁም ባሕር ዳር ለስፖርት፣ ለቱሪዝም እና ለቀጣናዊ ትብብር ማዕከል የሚያደርጋትን ትልቅ አቅም ለመመስከር ዕድል የሚሰጥ እንደነበር ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም