በአፍሪካ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማንበር ለወጣቶችና ሴቶች ተጠቃሚነት ልዩ ቦታ ሊሰጥ ይገባል - ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ - ኢዜአ አማርኛ
በአፍሪካ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማንበር ለወጣቶችና ሴቶች ተጠቃሚነት ልዩ ቦታ ሊሰጥ ይገባል - ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 14/2019 (ኢዜአ):-በአፍሪካ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማንበር ለወጣቶችና ሴቶች ተጠቃሚነት ልዩ ቦታ ሊሰጥ እንደሚገባ የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር እና የቡሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ገለጹ።
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብና ታላቅ ርዕይ
12ኛው የጣና ፎረም የመክፈቻ መርሐ ግብር በውቢቷ ባሕር ዳር በጣና ሐይቅ ዳርቻ "በአፍሪካ የሰላም መንገዶች፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የጂኦፖለቲካ ለውጥ" በሚል መሪ ሀሳብ መካሄድ ጀምሯል።
በአፍሪካ አህጉራዊ የሰላም መፍትሔ በማፍለቅ፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የጂኦፖለቲካ ለውጥ የዘንድሮው የጣና ፎረም የትኩረት አጀንዳዎች ናቸው።
የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር እና የቡሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ በዚህ ወቅት፤ አህጉራዊ ጸጋዎችን በማልማት የዜጎችን ሁለንተናዊ ደህንነት የሚያረጋግጥ የጋራ ዕድገት መገንባት አለብን ብለዋል።
አፍሪካ በርካታ ሀብቶች ያላት አህጉር መሆኗን በመግለጽ ፤ ሀብቷን ከግጭት ይልቅ ለሰላምና ለልማት ማዋል ይገባል ብለዋል።
ሰላምና ኢኮኖሚ የሚነጣጠሉ አይደሉም ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር እንደሚገባም ገልጸዋል።
በአፍሪካ ለጦርነት የሚውለውን ሀብት ለሰላም ማዋል እንደሚገባ ገልጸው፣ ለዚህ የሚበጅ ፖሊሲ መኖር አለበት ብለዋል።
ዘላቂ ሰላምና ቀጣይነት ያለው ልማት ለማረጋገጥ ወጣቶችና ሴቶች በሰላም ድርድርና ውይይት ላይ ቦታ እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ዓለም ፅንፍ የያዘችበት አውድ መፈጠሩን ገልጸው፤ ይህም አፍሪካውያንን ለክፍፍል እንዳይዳርገን አንድ ሆነን በአንድ ድምፅ መናገር አለብን ብለዋል።
በመሆኑም አፍሪካውያን ለሕዝብ ጥቅም የሚበጅ አጋርነት መፍጠር ይገባናል፣ የጸጥታው ምክር ቤትን በተመለከተ አፍሪካዊ አቋም መያዝ አለብን ብለዋል።