ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 14/2019 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ  አራተኛ ሳምንት  ሀዲያ ሆሳዕና ከፋሲል ከነማ  በሚያደርጉት ጨዋታ ጅማሮውን ያደርጋል።

ጨዋታው ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በአብዩ ኤርሳሞ ስታዲየም ይካሄዳል።

ሀዲያ ሆሳዕና ከሁለት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ በማግኘት 16ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

ተጋጣሚው ፋሲል ከነማ በሁለት ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ሁለቱም ቡድኖች በሊጉ የመጀመሪያ ድላቸውን ለማስመዝገብ ይጫወታሉ።

ቡድኖች በተመሳሳይ አንድ አንድ ቀሪ ጨዋታ አላቸው።

የአራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ይቆያል።

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከባህር ዳር ከተማ፣ ሲዳማ ቡና ከሃዋሳ ከተማ በአራተኛ ሳምንት ሊያደርጓቸው የነበሩ ጨዋታዎች በአህጉራዊ ጨዋታዎች ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፈዋል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሊጉን በሰባት ነጥብ እየመራ ይገኛል።

የባህር ዳር ከተማው አንተነህ ተፈራ በሶስት ግቦች የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን በመምራት ላይ ነው።

ጌታነህ ከበደ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ዳዊት ተፈራ (ሸገር ከተማ)፣ ሄኖክ ኤርሚያስ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) እና ቢኒያም ዐይተን (አዳማ ከተማ) በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም