ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የኃይል፣ የሠላም እና የጋራ ዕድገት ዋስትና ናት

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 13/2019 (ኢዜአ)፦‎ ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የኃይል አቅርቦት፣ የሠላም እና የጋራ ዕድገት ዋስትና መሆኗን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ጌታቸው ረዳ ገለጹ።

ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ

12ኛው የጣና ፎረም በውቢቷ ባህርዳር በጣና ሀይቅ ዳርቻ "በአፍሪካ የሰላም መንገዶች የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የጂኦ ፖለቲካ ለውጥ" በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ እየተካሄደ ነው።

በዘንድሮው የጣና ፎረም በአፍሪካ አሕጉራዊ የሰላም መፍትሔ በማበጀት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የጂኦ ፖለቲካ ለውጥ ማምጣት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ይደረጋል።

ፎረሙ አፍሪካን ከተቀባይነት ወደ አምራችነት ለማሸጋገር አሕጉራዊ ከፍተኛ ተቋማት በሚኖራቸው ሚና ላይም ይመክራል።


 

በቀይ ባህርና ምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ደህንነት ዙሪያ በምሥራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኞች የጣና ልዩ መልዕክተኞች ጉባኤ ተካሂዷል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ጌታቸው ረዳ  በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ የሚገኘው ለውጥ ለቀጣናው ሀገራት ወሳኝ ነው።

በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና ጸጥታ ጉዳዮች ለቀጣናው ሀገራት ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገች ያለች የ130 ሚሊዮን ዜጎች ሀገር መሆኗን በመጥቀስ፤ ዕድገቷ በቀጣናው ሀገራት ገንቢ ሆኖ መታየት እንዳለበት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የቀጣናው የሀይል አቅርቦት ማዕከል ብቻ አይደለችም ያሉት አቶ ጌታቸው፣ የአካባቢው የኢኮኖሚ የፀጥታና ደህንነት ዋስትና መሆኗንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በድንበር አካባቢ ለሰላምና ደህንነት የምታደርገውን ጥረት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በውል ሊረዳ ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም