ቀጥታ፡

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 13/2019 (ኢዜአ)፦‎ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የስምንተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ በኤፕስዊች ታውን እና ኖቲንግሃም ፎረስት መካከል ዛሬ ይደረጋል።

ጨዋታው ምሽት አራት ሰዓት ላይ በፖርትማን ሮድ ይካሄዳል።

ባለሜዳው ኤፕስዊች ታውን በዘጠኝ ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል።  ተጋጣሚው ኖቲንግሃም ፎረስት በአምስት ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

ሁለቱ ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለአምስተኛ ጊዜ ነው።

ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው አራት ጨዋታዎች ኖቲንግሃም ፎረስት ሁለት ጊዜ ሲያሸንፍ በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።

በአራቱ ጨዋታዎች ላይ ፎረስት ስምንት ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ኤፕስዊች ሶስት ጎሎችን አስቆጥሯል።

ክለቦች እ.አ.አ ማርች 15 2025 ለመጨረሻ ጊዜ በሊጉ በተገናኙበት ጨዋታ ኖቲንግሃም ፎረስት 4 ለ 2 አሸንፏል።

ኤፕስዊች ታውን በሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር በሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲ የ3 ለ 2 ሽንፈት አስተናግዷል።

ኖቲንግሃም ፎረስት ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ተሸንፏል።

ጨዋታው ሁለቱም ቡድኖች ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ነው።

ኤፕስዊች በፎረስት ላይ የመጀመሪያ የሊግ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል።

የ36 ዓመቱ የሼፍልድ ተወላጅ ቶም ብራሞል ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት እስከ ጥቅምት 15 2019 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም