ቀጥታ፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች የእውቅና እና ምስጋና መርሃ ግብር እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 12/2019 (ኢዜአ) ፦የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ያዘጋጀው የእውቅና እና ምስጋና መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።  

በመርሃ ግብሩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አህመድ ሽዴ፣ በምክር ቤቱ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ፍቃዱ ተሰማ፣ የምክር ቤቱ አባላት፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ጨምሮ  ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።


 

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምሁራን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሙያ ማህበራት፣ የመንግሥት ተወካዮች፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጨምሮ አሳታፊ በሆነ መልኩ ሰፋፊ ምክክሮችን በማድረግ የአጀንዳ ልየታ ስራ አከናውኗል። 

በዚህም ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ አራት ሺህ ተመካካሪዎችን ያሳተፈ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ተካሂዶ በስኬት ተጠናቋል።  

በምክክሩ ኮሚሽኑ 394 ምክረ ሃሳቦችን የለየ ሲሆን፤ ምክረ ሃሳቦችንም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስረክቧል።


 

ምክር ቤቱ ያዘጋጀውና  የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ምክክር ውጤታማ እንዲሆን ለሰላምና አንድነት መጠናከር እውቅና የሚሰጥ መድረክ እየተካሄደ ነው።


 

ምክር ቤቱ ያዘጋጀው የዛሬው መድረክ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ለሀገራዊ ምክክር ውጤታማ ሂደት ለነበራቸው ሚና እና ለሰላምና አንድነት መጠናከር እውቅና የሚሰጥ ነው።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም