መቻል እና ባህር ዳር ከተማ ድል ቀንቷቸዋል - ኢዜአ አማርኛ
መቻል እና ባህር ዳር ከተማ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 12/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብሮች ተካሄደዋል።
በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አባያ ካምፓስ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ መቻል ጋሞ ጨንቻን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ቲቶ ኦኬሎ በ44ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።
በሊጉ ሁለተኛ ድሉን ያስመዘገበው መቻል በስድስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አዳጊው ጋሞ ጨንቻ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን 18ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ጋሞ ጨንቻ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ አለው።
በሌላኛው መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ ወላይታ ድቻን 3 ለ 1 ረትቷል።
በሀላባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አንተነህ ተፈራ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ብሩክ ሰሙ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
መልካሙ ቦጋለ የወላይታ ድቻን ግብ አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ ባህር ዳር ከተማ በስድስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው ወላይታ ድቻ በሁለት ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ የሶስተኛ ሳምንት ግጥሚያዎች ተጠናቀዋል።
የአራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከጥቅምት 14 2019 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።