ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጓቸው ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ - ኢዜአ አማርኛ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጓቸው ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 12/2019 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ጨዋታዎች በመካሄድ ላይ ናቸው።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አዳማ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
አብዱልሃሚድ ሙባረክ ለቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ቢኒያም ዐይተን ለአዳማ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሁለት ነጥብ 12ኛ እና አዳማ ከተማ በአምስት ነጥብ 5ኛ ደረጃን ይዘዋል።
ሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ያከናወኑት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
ጌታነህ ከበደ በፍጹም ቅጣት ምት የሃዋሳ ከተማን ጎል ሲያስቆጥር ሎዌ ሎኛ የንግድ ባንክን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሰባት ነጥብ በሊጉ መሪነት ቀጥሏል። ሀዋሳ ከተማ በሁለት ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።