ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲና በሁሉ አቀፍ ልማት ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች የሀገርን ከፍታ ያሳዩ ናቸው

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 12/2019 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲና በሁሉ አቀፍ ልማት ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች የሀገርን ከፍታ ያሳዩ መሆናቸውን በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ተስፋዬ ገለጹ።

ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብና ታላቅ ርዕይ

"ሕብረት ወይስ ክህደት? ፀረ-ኢትዮጵያ ጥምረት ከየት ወዴት?" በሚል መሪ ሀሳብ በኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ እና በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት በጋራ የተዘጋጀ የፖሊሲ ውይይት ተካሂዷል።


 

በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ተስፋዬ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሀገር ውስጥ ባከናወነቻቸው የልማት ሥራዎች የኢኮኖሚ አቅሟን በማሳደግ በዲፕሎማሲው ዘርፍ የተሻለ አቅምና ስኬት ገንብታለች።

በተለይም በኢነርጂ፣ በግብርና፣ በምግብ ዋስትና፣ በኢኮኖሚ ልማትና በዲጂታላይዜሽን የተከናወኑ ሥራዎች የሀገሪቱን አቅም ከማሳደጋቸው ባለፈ በክልላዊና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ያላትን ሚና እያጠናከሩ መሆናቸውን አብራርተዋል።

በኢነርጂ ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎች ለጎረቤት ሀገራት የኃይል አቅርቦት እንዲስፋፋ በማድረግ የኢኮኖሚ ትስስርንና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማጠናከር አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ በኮሪደር ልማትና በዘመናዊ የከተማ ግንባታ ሥራዎች የቱሪዝምና የኮንፈረንስ መዳረሻነቷን ለማጠናከር ያላት አቅም ከፍተኛ መሆኑንም አስረድተዋል።

የሀገሪቱ የባህር በር የማግኘት ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ፣ በጋራ ጥቅምና በመስማማት መርህ ላይ ተመስርቶ እንዲመለስ መንግሥት በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም