ቀጥታ፡

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ህዝቡ መከላከያ ሰራዊትን በመደገፍ ያካሄደው ሰልፍ ለዘላቂ ሰላምና ልማት ያለውን ጠንካራ አቋም ያሳየበት ነው

ባህርዳር፣ጥቅምት 12/2019 (ኢዜአ) በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ህዝቡ መከላከያ ሰራዊትን በመደገፍ ያካሄደው ሰልፍ ለዘላቂ ሰላምና ልማት ያለውን ጠንካራ አቋም በተግባር ያሳየበት መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ገለጸ።

የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አባይ መንግስቴ፤ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተካሄደውን ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የህዝቡ የድጋፍ ሰልፍና በዚሁ አጋጣሚ ያስተላለፋቸው መልእክቶች ለክልሉ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ቀጣይነት ያለው እድገት ወሳኝ ስለመሆኑ አንስተዋል። 

በሁሉም አካባቢዎች የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ህዝቡ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያለውን ክብር፣ ፍቅርና አብሮነት በአደባባይ የገለጸበት መሆኑንም ተናግረዋል።

በመሆኑም በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ያካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ለዘላቂ ሰላምና ልማት ያለውን ጠንካራ አቋም በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል።

በሰልፉ ላይ የተንፀባረቁ መልእክቶች ለሰራዊቱ ከፍተኛ ክብርና ምስጋና ከማቅረብም ባለፈ በባንዳና ተላላኪነት የተሰለፉ አካላትን ያወገዙበት መሆኑንም ሃላፊው ገልጸዋል።

የክልሉ መንግስት የህዝቡን አቅም በመደመር በሁሉም ረገድ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ እድገትና ማንሰራራት ለማምጣት የሚሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም