ቀጥታ፡

የክልሉ መንግስት የልማት ጥረት እንዲሳካ የበኩላችንን እንወጣለን-የማረቆ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች

ቆሼ፤ ጥቅምት 12/2019 (ኢዜአ)፦ የክልሉ መንግስት የልማት ጥረት እንዲሳካና የጋራ ተጠቃሚነታችን እውን እንዲሆን የበኩላችንን እንወጣለን ሲሉ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማረቆ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ።

"በመደመር መንግስት በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚገኝ ዘላቂ ለውጥ" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በማረቆ ልዩ ወረዳ ቆሼ ከተማ ተካሂዷል።


 

በመድረኩ ላይ የተሳተፉ የልዩ ወረዳው ነዋሪዎች፤ የክልሉ መንግስት የልማት ጥረት እንዲሳካና የጋራ ተጠቃሚነታችን እውን እንዲሆን የበኩላችንን እንወጣለን ሲሉ አረጋግጠዋል።

ከመድረኩ የተሳታፊዎች መካከል ፓስተር ብርቱ ተፈራ፤ በክልሉ መንግስት የተያዙ የልማት እቅዶች መልካም መሆናቸውን አንስተው ለተግባራዊነቱና ለስኬቱ የሁላችንም እገዛ ያስፈልጋል ብለዋል።

የህዝቡን የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመመለስ የመንግስትን ዝግጁነት አድንቀው በጋራ ሰርተን ማሳካት ይኖርብናል ሲሉ አንስተዋል።

የክልሉ መንግስት የልማት እቅዶችና ሁለንተናዊ ጥረቶች ለስኬት እንዲበቁ አቅማችንን አሰባስበን ለመስራት ዝግጁ ነን በማለትም ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

ሌላኛው የመድረኩ ተሳታፊ አቶ ዴላ ግዛቱ፤ የመደመር መንግሥት ህዝቡ ቋንቋውን፣ ታሪኩንና ባህሉን እንዲያሳድግ እንዲሁም የልማት ተጠቃሚ እንዲሆነ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል።

በመሆኑም ለክልሉ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና የጋራ ተጠቃሚነት የሁላችንም ትብብርና እገዛ የሚያስፈለግ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ እንሰራለን ብለዋል።


 

የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)፤ የህዝቡ የሰላም ግንባታና የልማት ጥረት የሚበረታታ መሆኑን አንስተው ምርታማነትን በማሳደግ ከእርዳታ ጠባቂነት ለመውጣት በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

በክልሉ ባህላዊ እሴቶችን ለአስተሳሳሪ ትርክት ግንባታ በመጠቀም ለዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲሁም የጋራ ተጠቃሚነት መትጋት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል።፡ 

በዚህ ረገድ የመደመር መንግስት በቁርጠኝነትና በተሟላ ዝግጁነት የሚሰራ መሆኑን አረጋግጠው በተደመረ አቅም ለእድገትና ማንሰራራት መትጋት ይኖርብናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም