ጽምዶ ስሁት ፕሮፓጋንዳን በማሰራጨት ሕዝብን ለማወናበድ የሚሞክር መሠረተ ቢስ ስብስብ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ጽምዶ ስሁት ፕሮፓጋንዳን በማሰራጨት ሕዝብን ለማወናበድ የሚሞክር መሠረተ ቢስ ስብስብ ነው
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 12/2019 (ኢዜአ)፦ጽምዶ ስሁት ፕሮፓጋንዳን በማሰራጨት ሕዝብን ለማወናበድ የሚሞክር መሠረተ ቢስ ስብስብ መሆኑን በተግባር ያሳየ ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ገለጹ ።
"ሕብረት ወይስ ክህደት? ፀረ-ኢትዮጵያ ጥምረት ከየት ወዴት?'' በሚል መሪ ሀሳብ በኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ እና በዉጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት በጋራ የተዘጋጀ የፖሊሲ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የጽምዶ ጥምረት የተደራጀ አቅም ሳይኖረው የተመሠረተ እና ስሁት ፕሮፓጋንዳን በማሰራጨት ሕዝብን ለማወናበድ የሚሞክር መሠረተ ቢስ ስብስብ ነው።
በተለይም ሕገ-ወጡ ሕወሓት ከፋኖ፣ ሸኔና ሌሎች ኃይሎች ጋር የሚያደርገው ግንኙነት በጥላቻና በተለያዩ ጥቅሞች ዙሪያ የተፈጠረ ጥምረት መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ምላሽ አገራዊ ስትራቴጂካዊ ጥቅሞችን ለማስከበርና አላስፈላጊ ጉዳቶችን ለመቀነስ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።