በተጠባቂው ጨዋታ ግብር ባየር ሙኒክ እና አርሰናል አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው ጨዋታ ግብር ባየር ሙኒክ እና አርሰናል አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 11/2019 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተጠባቂ መርሐ ግብር ባየርሙኒክ እና አርሰናል ያደረጉት ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
ማምሻውን በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አልፎንሶ ዴቪስ እና ሃሪ ኬን (ፍጹም ቅጣት ምት) ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ኤበሬቺ ኤዜ እና ዴክላን ራይስ የአርሰናልን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ጨዋታው አዝናኝ እና ተመጣጣኝ ፉክክር ተደርጎበታል።
አርሰናል በሰባት ነጥብ 7ተኛ እና ባየር ሙኒክ በአምስት ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
በሌላኛው መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ አርቢ ላይፕዚግን 4 ለ 1 ረትቷል።
በበርናባው ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ በርናንዶ ሲልቫ፣ አርዳ ጉለር፣ ኪሊያን ምባፔ እና ያን ዲዮማንዴ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ቲዲያም ጎሚስ ለጀርመኑ ክለብ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
የ15 ጊዜ የዋንጫው ባለቤት ማድሪድ በዘጠኝ ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
አስቶንቪላ ቫይኪንግን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ኢሚሊያኖ ቡንዲያ፣ ሮስ ባርክሌይ እና የቫይኪንጉ ሄነሪክ ሄግሄም በራሱ ላይ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ፒተር ክሪስቲያንሰን የቫይኪንግን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
አስቶንቪላ በዘጠኝ ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
ኢንተር ሚላን ሻካታር ዶኔስክን እና ሪያል ቤቲስ ፌይኖርድን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል።
ክለብ ብሩዥ ሌንስን 3 ለ 0፣ ላስክ ስፖርቲንግ ሊዝበንን 3 ለ 2 አሸንፈዋል።
ዛሬ አስቀድመው በተደረጉ ጨዋታዎች ኮሞ ማንችስተር ዩናይትድን 4 ለ 1 እና ጋላታሳራይ ሊልን 4 ለ 2 ረትተዋል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ የሶስተኛ ዙር ጨዋታዎች ተጠናቀዋል።
የአራተኛ ዙር መርሐ ግብር ጥቅምት 24 እና 25 2019 ዓ.ም ይካሄዳል።