ኢትዮጵያ በአፍሪካ የጎዳና ብስክሌት ሻምፒዮና መክፈቻ ሁለት ሜዳሊያዎችን አገኘች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በአፍሪካ የጎዳና ብስክሌት ሻምፒዮና መክፈቻ ሁለት ሜዳሊያዎችን አገኘች
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 11/2019 (ኢዜአ) ፦ የ2026 የአፍሪካ የጎዳና ብስክሌት ሻምፒዮና ዛሬ በኬንያ ኪሱሙ ተጀምሯል።
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ላይ እየተሳተፈች ነው።
በውድድሩ መክፈቻ ቀን በወጣት ሴቶች የግል ሰዓት ሙከራ ራሔል ጊምባቶ ሶስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች።
ቅሳነት ግርማይ ሰባተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
ከ23 ዓመት በታች በተካሄው የግል ሰዓት ሙከራ ውድድር የተሳተፈችው ፅጌ ካህሣይ ሶስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች።
በአፍሪካ የጎዳና ብስክሌት ሻምፒዮና ከ32 ሀገራት የተወጣጡ 354 ብስክሌተኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ሻምፒዮናው እስከ ጥቅምት 15 2019 ዓ.ም ይቆያል።