ቀጥታ፡

ነገሌ አርሲ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 11/2019 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት ነገሌ አርሲ ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 0 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ገብረመስቀል ዱባለ በጨዋታ እንዲሁም ዳዊት ተፈራ እና ጋናዊው ኮሊንስ ኮፊ በፍጹም ቅጣት ግቦቹን አስቆጥረዋል።




የኢትዮጵያ ቡናው ተከላካይ ድልአዲስ ገብሬ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።

በጨዋታው ነገሌ አርሲ የተሻለ እንቅስቃሴ አድርጓል።

በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድሉን ያስመዘገበው ነገሌ አርሲ በአምስት ነጥብ ደረጃውን ከ11ኛ ወደ 2ኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በሊጉ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በሶስት ነጥብ ከነበረበት 7ኛ ደረጃ ወደ 10ኛ ዝቅ ብሏል።

በአራተኛ ሳምንት ነገሌ አርሲ ከአዳማ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም