ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ቡና ከነገሌ አርሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 11/2019 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከነገሌ አርሲ ዛሬ ይጫወታሉ።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል።

ኢትዮጵያ ቡና በሶስት ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል። ነገሌ አርሲ በሁለት ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ቡናማዎቹ በሁለተኛ ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 1 ማሸነፋቸው ይታወሳል።

ነገሌ አርሲ በሁለቱ የሊጉ ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል።

ኢትዮጵያ ቡና ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ፣ ነገሌ አርሲ የመጀመሪያ ሶስት ነጥቡን ለማግኘት የሚያደርጉት ጨዋታ ተመጣጣኝ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የሁለቱ ቡድኖች ደጋፊዎች ሌላኛው የጨዋታው ድምቀት ናቸው።

ቡድኖቹ በ2018 ዓ.ም ባደረጓቸው ሁለት የሊግ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡና ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም