ቀጥታ፡

ባየር ሙኒክ ከአርሰናል፣ የሻምፒዮንስ ሊጉ ተጠባቂ መርሐ ግብር

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 11 /2019 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ዘጠኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ምሽት አራት ሰዓት ላይ ባየር ሙኒክ እና አርሰናልን በአሊያንዝ ስታዲየም የሚያገናኘው ጨዋታ የእግር ኳስ ቤተሰቡን ትኩረት ስቧል።

ባለሜዳው ባየር ሙኒክ እስከ አሁን ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች በአራት ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።

የባለፈው ዓመት ፍጻሜ ተፋላሚ አርሰናል ሁለቱንም የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች በድል ተወጥቷል። በስድስት ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ሁለቱ ክለቦች በሻምፒዮንስ ሊጉ ሲገናኙ የአሁኑ ለ16ኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 15 ጨዋታዎች ባየር ሙኒክ ስምንት ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ይዟል። አርሰናል አራት ጊዜ ድል ሲቀናው በቀሪ ሶስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።

ባየር ሙኒክ በ15ቱ ጨዋታዎች ላይ 31 ግቦችን ሲያስቆጥር አርሰናል 18 ግቦችን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ቡድኖቹ በውድድሩ ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት እ.አ.አ በ2025/26  በሊግ ምዕራፍ መርሐ ግብር ላይ ነው።  አርሰናል ጨዋታውን 3 ለ 1 አሸንፏል።

ባየር ሙኒክ የሻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ ስድስት ጊዜ አንስቷል። አርሰናል ውድድሩን አሸንፎ አያውቅም።

ሁለቱ ቡድኖች ለእግር ኳስ ቤተሰቡ አዝናኝ እና ጠንካራ ፉክክር ያሳያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በሌሎች መርሃ ግብሮች ሪያል ማድሪድ ከአርቢ ላይፕዚግ፣ኢንተር ሚላን ከሻካታር ዶኔስክ፣ አስቶንቪላ ከቫይኪንግ፣ ሪያል ቤቲስ ከፌይኖርድ ሮተርዳም፣ ክለብ ብሩዥ ከሌንስ እና ስፖርቲንግ ሊዝበን ከላስክ በተመሳሳይ ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ኮሞ ከማንችስተር ዩናይትድ እና ሊል ከጋላታሳራይ በተመሳሳይ ከምሽቱ 1 ሰዓት ከ45 ላይ ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም