ቀጥታ፡

በተጠባቂው ፍልሚያ ፒኤስጂ ባርሴሎናን አሸነፈ


አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተጠባቂ መርሐ ግብር ፒኤስጂ ባርሴሎናን 4 ለ 2 አሸንፏል።


ማምሻውን በፓርክ ደ ፕሪንስ በተካሄደው ጨዋታ ዴዚሪ ዱዌ ፣ቲኦ ሄርናንዴዝ፣ ቪትንሃ እና ፋቢያን ሩዊዝ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ዣቪ ኤስፓርት እና ላሚን ያማል ለባርሴሎና ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

በጨዋታው ፒኤስጂ በጨዋታው ተጨማሪ ግቦችን ማስቆጠር የሚችልባቸውን እድሎች አልተጠቀመም።

ጨዋታው አዝናኝ እና ማጥቃት ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴ ታይቶበታል።

ፒኤስጂ ሶስተኛ ድሉን በማስመዝገብ በዘጠኝ ነጥብ  በመሪነቱ ቀጥሏል። ቡድኑ የባለፉት ሁለት የሻምፒዮንስ ሊግ ውድድሮች አሸናፊ ነው።

በሻምፒዮንስ ሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው ባርሴሎና በስድስት አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በውድድር ዓመቱም ለመጀመሪያ ጊዜ ተሸንፏል።

በሌላኛው መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ኤኢኬ አቴንስን 5 ለ 1 ረትቷል።

ፊል ፎደን ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል። ሪያን ቸርኪ እና ኤሊዮት አንደርሰን ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ስታቭሮስ ፒሊዮስ ለኤኢኬ አቴንስ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።

ሊቨርፑል ከ2 ለ 0 መመራት ተነስቶ 4 ለ 3 አሸንፏል።

አሌክሲስ ማካሊስተር ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ፍሎሪያን ዊርትዝ እና ሮናልድ አራውሆ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ጋር አገናኝተዋል።

ሊቨርፑል በዘጠኝ ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

ሮማ ስሎቫን ብራቲስላቫን 4 ለ ዐ፣ ናፖሊ ቦዶ ግሊምትን 4 ለ 2  እና ፒኤስቪ አይንድሆቨን ፖርቶን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።

ስቱትጋርት እና አትሌቲኮ ማድሪድ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም