ቀጥታ፡

ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሶስተኛ ዙር ጨዋታዎች ማምሻውን መካሄድ ጀምረዋል።

በባኩ ኦሊምፒክ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ሳባህን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ጊኒያዊው አጥቂ ሴርሁ ጉይራሲ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥሯል።

ኤደን ማካርቲን የሳባህን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ዶርትሙንድ ሁለተኛ ድሉን አግኝቷል።

ሳባህ ሁለተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

በሌላኛው መርሐ ግብ ፊነርባቼ ከስላቪያ ፕራግ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

ኦጉዝ አይዲን እና ሜሰን ግሪንውድ የፊነርባቼን ጎሎች አስቀጥረዋል።

ሉካስ ፕሮቮድ እና ፓቬል ካሶር የስላቪያ ፕራግን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ፊነርባቼ በዘንድሮው ውድድር ለሁለተኛ ጊዜ አቻ ወጥቷል።

ስላቪያ ፕራግ የመጀመሪያ ነጥቡን አግኝቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም