ቀጥታ፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ

አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሸገር ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጋቦናዊው ካሌብ ስቴፍ ሜልቪን በሶስተኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።

በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በአራት ነጥብ ደረጃውን ከ16ኛ ወደ 5ኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈት ያስተናገደው ሸገር ከተማ በተመሳሳይ አራት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ 6ኛ ደረጃን ይዟል።

በአራተኛ ሳምንት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ሸገር ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም