ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በኤልዶሬት ቤተመንግስት አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በኤልዶሬት ቤተመንግስት አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በኤልዶሬት ቤተመንግስት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ በመሳተፍ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኬንያ ነፃነት፣ ሉዓላዊነትና ልማት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ጀግኖች ክብር በሚሰጥበት የማሹጃ ቀን (የጀግኖች ቀን) ብሔራዊ በዓል አከባበር ላይ በክብር እንግድነት በመገኘትና ንግግር በማድረግ፤ ለሀገራቸው ነጻነት ለታገሉና ሉዓላዊነታቸውን ለማስከበር ታላቅ መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች ያላቸውን ታላቅ ክብር መግለጻቸው ይታወሳል።