የ2019 ዓ.ም የሐጅ ጉዞ ምዝገባ የፊታችን ሐሙስ ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
የ2019 ዓ.ም የሐጅ ጉዞ ምዝገባ የፊታችን ሐሙስ ይጀመራል
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2019 ዓ.ም የሐጅ ጉዞ ምዝገባ የፊታችን ሐሙስ እንደሚጀምር አስታወቀ።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2019 ዓ.ም የሐጅ ጉዞ ምዝገባ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
ምክር ቤቱ ምዝገባውን ግልጽ፣ ቀልጣፋ እና ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ አገልግሎቱን ማዘመኑን ገልጸው፣ ሕዝበ ሙስሊሙ ምዝገባውን እንዲያከናውን ጥሪ አቅርበዋል።
በጠቅላይ ምክር ቤቱ የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ የዘንድሮው የምዝገባ ሂደት ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ እንግልቶችን በሚያስቀርና የኢትዮጵያን ሙስሊም እንዲሁም የነጃሺን ታሪክ በሚመጥን መልኩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
ምክር ቤቱ ባለፈው ዓመት ባቀረበው የላቀ አገልግሎት ከሳዑዲ አረቢያ የ"ዳይመንድ ደረጃ" (Diamond Award) ሽልማት ማግኘቱንም ጠቅሰዋል።
የምዝገባ ሂደቱ ቴክኖሎጂን በሚጠቀሙ 33 የሐጅ ምዝገባ ማዕከላት በኩል እስከ ጥር 10 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ገልጸዋል።