ቀጥታ፡

የትግራይ ህዝብ አንድነቱን እና ተቋማቱን ጠብቆ ለሰላምና ለልማት በጋራ ሊቆም ይገባል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ የትግራይ ህዝብ አንድነቱን እና ተቋማቱን ጠብቆ ለሰላምና ለልማት በጋራ እንዲቆም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በትግርኛ ቋንቋ ቆይታ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኘው የትግራይ ህዝብ ለዘላቂ ሰላም ግንባት እንዲተጋ ጠይቀዋል።

እናቶች ከልጆቻቸው ጋር እንዲገናኙ እንዲሁም የተጎዳው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት እንዲነቃቃ በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል።

በሌላ በኩል የታጠቁ ወጣቶች ትጥቃቸውን አስረክበው ወደ ተሃድሶ (ዲዲአር) ስርዓት እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ወታደራዊና ፖለቲካዊ መሪዎችም በሰላም እጃቸውን እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

በምርጫ መደበኛ አስተዳደር እስኪመሰረት ድረስም የህዝቡን ደህንነትና ሰላም የማረጋገጡ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።

የትግራይ ህዝብ ወደ መሪዎች ምርጫ፣ ወደ እርሻና መስኖ ልማት፣ እንዲሁም ወደ ማዕድን እና ኢንዱስትሪ ልማት መግባት እንዳለበት አሳስበዋል።

የትግራይ ከተሞች ደግሞ ወደ ኮሪደር ልማት መግባት እንዳለባቸውም ገልጸዋል።

ለሕዝባችን የሚገባው ሰላምና ዳግም ግንባታ በመሆኑ፣ ይህንኑ ለማሳካት ከትግራይ ሕዝብ ጋር በቅንጅት እንሰራለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም