ቶተንሃም ሆትስፐርስ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ቶተንሃም ሆትስፐርስ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቶተንሃም ሆትስፐርስ ኮቨንተሪ ሲቲን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጀምስ ማዲሰን፣ ኦማር ማርሙሽ እና ቤን ዴቪስ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ጃክ ሩዶኒ የኮቨንተሪ ሲቲን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ባለሜዳው ስፐርስ በጨዋታው የተሻለ እንቅስቃሴ አድርጓል።
በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድሉን ያስመዘገበው ቶተንሃም ሆትስፐርስ በስድስት ነጥብ ከነበረበት 20ኛ ደረጃ ወደ 16ኛ ከፍ በማለት ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ የናፈቀውን ድል አግኝቷል።
በሊጉ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አዳጊው ኮቨንተሪ ሲቲ በተመሳሳይ ስድስት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ 17ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በስምንተኛ ሳምንት ቶተንሃም ከቼልሲ፣ ኮቨንተሪ ከፉልሃም ይጫወታሉ።
የዛሬውን ጨዋታ ተከትሎ ሰባተኛ ሳምንት ተጠናቋል።
የስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።