ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በትግርኛ ቋንቋ ባደረጉት ቆይታ ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በትግርኛ ቋንቋ ባደረጉት ቆይታ ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-

👉 ከሕዝባችን ጋር ሆነን ለመልሶ ግንባታና ለሰላም እንሠራለን። ይህ ነው ለትግራይ ሕዝብ የሚገባው።

👉በውጭ ያለውም ሆነ በውስጥ ያለው ትግራዋይ ሁሉ እንደ ሕዝብ ወደ ሰላም ይመለስ።

👉እናቶች ከልጆቻቸው ጋር ይገናኙ። የተጎዳው ኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ይነቃቃ።

👉በምርጫ መደበኛ አስተዳደር እስኪመሰረት ድረስ ሕዝባችን አንድነትህንና ተቋማትህን ጠብቅ።ከጸጥታ አካላት ጋር ተባብረህ ሥራ።

👉የትግራይ ሕዝብ በህወሓት ምክንያት እጅግ ብዙ ዋጋ ከፍሏል

👉የታጠቃችሁ ወጣቶች ትጥቃችሁን አስረክቡ።በሰላም እጃችሁን ሰጥታችሁ ወደ DDR ሥርዓት ግቡ።ወታደራዊና ፖለቲካዊ መሪዎች በሰላም እጃችሁን ስጡ። ይበቃናል ሰላም ይሻለናል።

👉የትግራይ ሕዝብ መሪዎችህን ወደ መምረጥ፣ወደ እርሻና መስኖ ልማት፣ ወደ ማዕድንና ኢንዱስትሪ ልማት፣ የትግራይ ከተሞች ወደ ኮሪደር ልማት ይግቡ

👉የሕወሓት መሪዎች ተመችቷቸው እየኖሩ የትግራይ ወጣት መሞት የለበትም

👉ሕወሓት መርህ የለውም፤ በአፍ ሕዝባዊ ይመስላል፣ በተግባሩ ግን ፀረ-ሕዝብ ነው።

👉የትግራይ ህዝብ አንድነቱን እና ተቋማቱን ጠብቆ ለሰላምና ለልማት በጋራ ሊቆም ይገባል የሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለትግራይ ሕዝብ ያስተላለፏቸው መልዕክቶች ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም